Description
የሰላማዊ ትግል እርምጃ ተራ ሰዎች ለመብቶቻቸው፣ ለነጻነት እና ለፍትህ የሚፋለሙበት መንገድ ነው። ብዙ ጊዜ ከምግባራዊና ግብረገባዊ ሰላማዊ ትግል ጋር ተያይዞ የሚታይ ቢሆንም፥ እዚህ ጽሁፍ ላይ፣ በግጭት ወቅት ተጽህኖ ለመፍጠር እንደሚያስችል ተጨባች መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ለማስፋት፥ ከሌሎች ምግባራዊና ግብረገባዊ መሰረቶች ተለይቶ፣ ራሱን እንደቻለ ክስተት ተመልክቼ ለማየት እሞክራለሁ።